Video medium

የደቡብ ሱዳን አማፂ ቡድን መሪ ሪክ መቻር አዲሱን የሰላም ስምምነት ውድቅ አደረጉ

By Admin

August 28, 2018

የደቡብ ሱዳኑ አማፃ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በሀገሪቱ ያለውን የእርስ በእርስ ግጭት ፍፃሜ ያበጃል ተብሎ የተጠበቀውን የሰላም ስምምነት ውድቅ ማድረጋቸውን  የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፈው ወር የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ሪክ ማቻር የተኩስ አቁም  እና የስልጣን መጋራት እንዲኖር የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

ሆኖም ሪክ ማቻር አዲስ የተዘጋጀውን የሰላም ስምምነት ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፥ ይህም ወደ ሙሉ ስምምነት ለመድረስ የሚደረገው ጥረት አዳጋች እንደሆነ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አል ዲርዲር መሀመድ፥ ዋነኛው የአማፂ ቡድን መሪ ሪክ ማቻርን ጨምሮ ሌሎች አማፂ ቡድኖች ከተለያዩ ጥቃቶች እንዲቆጠቡ የሚያስችለውን ስምምነት ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

በደቡብ ሱዳን ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ሀገሪቱ ነፃነቷን ከአወጀች ሁለት አመታት በኋላ በፈረንጆቹ 2013 የተጀመረ ሲሆን፥ 12 ሚለየን የሚሆነው የሀገሪቱ ዜጎች ከመኖሪያቸው ቄያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።

ምንጭ፥ ሲጂቲኤን