Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

0 1,248

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ እና የሀገሪቱ ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ስለኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ግንኙነት እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ በነገው ዕለት አዲስ አበባ ይገባሉ።
 
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት አቡደል ፈታ አልሲሲ የተላከውን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያደርሳሉ ተብሏል።
 
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ እና ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በፈረንጆቹ 2015 በአባይ ወንዝ ዙሪያ ስለደረሱበት ስምምነት አፈፃፀም ውይይት ያደርጋሉ ነው የተባለው።
 
ከዚህ ባለፈ በሶስቱ ሀገራት ለመሰረተ ልማት  ኢንቨስትመንት የሚውል ፈንድ ለማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
 
እንዲሁም የሶስቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ግንቦት ወር በአሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዎች ላይ ስለደረሱባቸው ስምምነት ውይይት እንደሚያደርጉ ታውቋል።
 
በሀገራቱ መካከል የተደረሰው ስምምነት የታላቁ ህዳሴ ግድብን የሚከታተል አለም አቀፍ ባለሙያዎች ያካተተ ኮሚቴ ማዋቀር የሚያስችል እንደነበር ተነግሯል።
 
የሶስቱ ሀገራት መሪዎች በየስድስት ወሩ ለምክክር እንዲገናኙ በሀገራቱ መካከል በተደረሰው ስምምነት መግባባት ላይ መደረሱን አልሀራም በዘገባው አስታውሷል።
FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy