Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋ ተከፈተ

0 665

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፍቶ ስራ ጀመረ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲውን በዘሬው እለት መርቀው ከፍተዋል።

ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተዘግቶ የቆየው በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በዛሬው እለት ዳግም በይፋ ስራውን ጀምሯል።

በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።

ኤርትራ በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መክፈቷ ይታወሳል።

ባለፈው ሃምሌ ወር የተከፈተው የኤርትራ ኤምባሲ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

fbc

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy