Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ትምህርት ለሀገር ዕድገት

0 2,667

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ትምህርት ለሀገር ዕድገት

                                                                  ዮሰን በየነ

ትምህርት ለአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና አለው።ምክንያቱም ለአገር ዕድገት መፋጠንም ሆነ ወደ ኋላ መዘግየት በአገሪቱ የሚኖሩ የተማሩ  ህዝቦች ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።ታዲያ አፄ ሚኒሊክ ይህን ነገር በደንብ የተረዱት ይመሳላል ንጉሡ በወቅቱ ለዘመናዊ ትምህርት ከፍተኛ ቦታ ሰጥተው ሲሰሩ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ነገር ነው። አፄ ሚኒሊክ በዘመናቸው ዘመናዊ ትምህርት በሀገራችን እንዲጀመር ያደረጉ ግንባር ቀደም መሪ ነበሩ።ዘመናዊ ትምህርት አንድ ሁለት እያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸሻለ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሶዋል።ይህ በአፄ ሚኒሊክ የተጀመረው ዘመናዊ ትምህርት አሁን ላይ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል።

ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የነበረው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀትና የተማሪዎችን ተሳትፎ ስንመለከት 4ሺህ የመጀመሪያና 278 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የነበሩ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ከሁለት ሚሊዮን ያልበለጡ ተማሪዎችን ብቻ  ያስተናግዱ ነበር። በዚህም ሀገራችን ከዓለም ሀገራት መካከል በትምህርት ቤቶች ተደራሽነት በዝቅተኝነት ተጠቃሽ አድርጓት እንደነበር በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ለውይይት ያቀረበው ፍኖተ ካርታ ላይ ይጠቁማል።  

ከደርግ ውድቀት ወዲህ ባሉት 24 ዓመታት ግን  በሁሉም አካባቢዎች የተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ተማሪዎች በአፍ መፍቻ  ቋንቋቸው የመማር ዕድሎችን አግኝተዋል።ትምህርትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ከ39 ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃና 3ሺህ300 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው የተማረ ዜጋን ለመፍጠር መንግሥት ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከ28 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይችላሉ። በደርግ ዘመን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ ሁለት ብቻ የነበሩት ዩኒቨርስቲዎቻችን አሁን ላይ ግን በተለያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተስፋፍተው 46 ደርሰዋል ።በተጨማሪም 130 የሚሆኑ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከፍተው ከፍለው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሯል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የትምህርት ተደራሽነቱ በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋቱ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት የትምህርት ዕድሎችን በማመቻቸት ተማሪዎችን ተቀብላ በማስተማር ላይ ትገኛለች።ለአብነት ያህል ከሱዳን፣ከጅቡቲና ከሶማሊያ ተማሪዎችን ተቀብላ በማስተማርና በማስመረቅ ላይ ።

በሀገራችን ምሁራን ረቂቅ ጥናት ሰነድ በትምህርትና ሥልጠና ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫ ዙሪያ ተጠንቶ ካለፈው ሣምንት በፊት ለውይይት የቀረበው ፍኖተ ካርታ ለቀጣይ 15 ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴርም ለሠራተኞቹ ስለ ፍኖተ ካርታው ምንነት በቂ ግንዛቤን እንዲኖራቸው ስለረቂቅ ሰነዱ ዝግጅት ሂደትና ሰነዱ ስላ ቀረባቸውን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ጉድለቶችና አማራጭ ሀሳቦች በአጥኚ ቡድኖችና ምሁራን በቂ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል።ሠራተኞቹም ስለ ፍኖተ ካርታው በቂ ግንዛቤን ማግኘታቸውን ገልፀዋል።ጥናቱ የተዘጋጀው በሀገር በቀል ከፍተኛ ምሁራን ስለሆነ በትምህርት ዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውን በስፋት የሚዳስሳ ነው።

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ክቡር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ  የፍኖተ ካርታው ዝግጅት ጥናት ረቂቅ ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችና  አመራሮች ቀርቦ ውይይት በተደረገበት ወቅት እንደገለፁት የጥናት ሰነዱ በቀጣዩ የትምህርት ሳምንት በየደረጃው በስፋት ውይይት እንደሚደረግበትና ለቀጣይ 25 ዓመታት እንደሚተገበር ለተሳታፊዎች ገልፀዋል።በተጨማሪም የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮችም በአጥኚዎቹ ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለፍኖተ ካርታው ዝግጅት የሚረዱ ጠቃሚ ምክር ሃሳቦች ፣ የማሻሻያና የመፍትሄ  አስተያየቶችን በማቅረብ የየድርሻቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።የትምህርትና የስልጠና ፖሊሲው ባለፉት ዓመታት በርካታ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ቢኖሩም ችግሮችም የዛኑ ያህል ነበሩበት ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት ይህንን ችግር ሊፈታ የሚችል ጥናት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማስጠናት ይህንን ረቂቅ የጥናት ሰነድ ማዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ አክለው ገልፀዋል።አገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዘላቂ የልማት ልማት ግቦች ከትምህርት ና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ጋር በማስተሳሰር ለትምህርት ልማት ግቦች መሳካት ርብርብ ማድረግ ይገባል።

ይህንን ረቂቅ ጥናት ውጤታማ ለማድረግ ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በማስተሳሰር ድህነትን ለማጥፋት፣ ጤናማ ህብረተሰብን ለመፍጠር፣የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥና ለሁሉም ለማዳረስ እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ ሁሉም ኅብረተሰብ የሚጠበቅበትን በመወጣት በሁሉም መስከ የተሳካላት ኢትዮጲያን ለመፍጠር መረባበብና የተጀመረውን የለውጥ ጅማሮ ማስቀጠል ይገባል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy