Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ችግሩ እንዲቀረፍ

0 313

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ችግሩ እንዲቀረፍ

ገናናው በቀለ

በየአካባቢው በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ችግሮች እየተፈቱ ነው። አሁንም ችግሮችን በተጠናከረ ሁኔታ ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ አቋም ይዟል። በህዝቡ ውስጥ የሚታየውን ስሜት በቅርበት በመረዳት ችግሩን ከህዝቡ ፍላጎት አኳያ ሚዛን እየሰጡ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው።

ከመልካም አስተዳደር አኳያ በአሁኑ ሰዓት እየተከናወኑ ያሉት ችግሮች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው። ለምሳሌ ያህል በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የተሾሙ የስራ ኃላፊዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በጀመሩት እንቅስቃሴ ለውጥ እያመጡ ነው። በየክፍለ ከተማው የሚገኙ አስፈጻሚዎችን ምደባ የማስተካከል፣ ከህዝቡ ጋር ፊት ለፊት ተቀራርቦ የመነጋገር፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ለመፍጠርና ሌሎች ተግባሮችን ለማከናወን እያደረጉት ያለው ጥረት ሊጠቀስ የሚገባው ነው።

የዚህ ድምር ውጤትም እንደ አገር በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ የተቀመጡትን ዕቅዶች ለማሳካት የሚያስችል ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ በአሁኑ ሰዓት የግልፅነትና የተጠያቂነት አሠራርን በማስፈን የኪራይ ሰብሳብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትን ለመቀነስ በየደረጃው የሚደረጉ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ የህብረተሰብ ተሳትፎ የሚጠናከርበትና ከመንግስት ተቋማት ጋር ቋሚ ግንኙነት የሚፈጥርበት አሰራርም ተዘርግቷል፡፡

በተለይም የሀገራችን ህዳሴ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ የሚታሰበውን ሙስናንና ኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብና ድርጊት ለመከላከል ሲባል መንግስት የራሱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ሳይቀር በህግ ፊት በማቅረብ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል። በዚህም አስተማሪ በሆነ መንገድ ትምህርት ለመስጠት ሞክሯል።

ምንም እንኳን የሙስና ችግር በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችል ባይሆንም፣ ድርጊቱን በሂደት የመቅረፍ ስራዎች ይከናወናሉ። በዚህም አዳዲስ አሰራሮችን ለመተግበር ታቅዷል።

በዕቅዱ የዜጐችን እኩል የልማት ተሳታፊነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና አንድ አገርን ለመገንባት ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡ ይህ ትኩረትም በጥናት ላይ በመመርኮዝ በመልካም አስተዳደር ጉዳዩች ላይ ተገቢውን እርምት ማድረግ ያስችላል፡፡

የፖለቲካ ኢኮኖሚው ሙስና የበላይነት ከያዘበት ወደ ልማታዊነት የበላይነት ወደ ያዘበት መሸጋገሩ እንዲሸጋገር ያደርጋል። ስለሆነም በአንድ ወገን ልማታዊነትን የሚያጐለብቱ ድጋፎችን በጥራት በማቅረብ፣ በሌላ በኩል የሙስና ዋነኛ ምንጭ ሆነው የተለዩትን ጉዳዮች በልዩ ትኩረት በማድረቅ ብልሹ አሠራሮችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ልማታዊነት የበለጠ እንዲጐመራና የአንበሳውን ድርሻ እንዲይዝ ማድረግ ይቻላል። ይህም መልካም አስተዳደርን ዕውን ከማድረግና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እጅግ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የለውጥ አመራሩና ህዝቡ ችግሩን በሂደት ለመፍታትና መልካም አስተዳዳርን ለማስፈን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ህብረተሰቡን በተደራጀ መልኩ የማንቀሳቀስ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካም ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ እስሁን ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ ቢሆኑም አሁንም ጠንካራ ሥራ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

ኢኮኖሚውን ለመገንባትና መንግስት በቀይ መስመርነት ያስቀመጠውን ሙስናን ለማዳከም ከውጭ ምንዛሬ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ከሌሎች መልካም አስተዳደርን ከሚያዛቡ ጉዳዩች አኳያ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

ያም ሆኖ ሁሉንም ነገር በመንግስት ላይ ብቻ በመጣል ውጤት ማምጣት ስለማይቻል በአዲሱ ዓመት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ ህብረተሰቡም የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ህብረተሰቡ የለውጡ ባለቤት በመሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የለውጥ አመራሩና የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው ከህዝቡ ጋር በተደራጀ መንገድ በመቀናጀት መስራት ይኖርባቸዋል። ለዚህም ስራው የእገሌ ነው ሳይባል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።

እርግጥ አገራችን አረጋግጠዋለሁ ብላ ለተነሳችው የለውጥ ሂደት ሙስና አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይም ሙስናን ቀይ መስመር ነው ያሉት ለዚሁ ነው። እናም አደጋዎቹን ለመዋጋትና ትግሉን በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ እሳቤ የበላይነት ለመደምደም በርካታ ስራዎችን ማከናወን የግድ በመሆኑ በዕቅዱ ተይዟል።

በዕቅድ ዘመኑ ማንኛውም ተቋም በአሰራሩና በአደረጃጀቱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥን ባልተሸራረፈ መልኩ በመከተልና የአገልግሎት አሰጣጡም ተገልጋዮችን የሚያረካ፣ ቀልጣፋና ተልዕኮውን በተሟላ ውጤታማነት መፈጸም እንዲችል አስፈላጊው ክትትልም ሆነ ድጋፍ ለማድረግ ታቅዷል። የውጤት ተኮር ስርዓት ትግበራው የተጠናከረ የመንግስት የአፈጻጸም አመራር ማዕቀፍ እንዲሆንም ይደረጋል። እየተደረገም ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ መልካም አስተዳደርን የማረጋገጥ ጉዳይ ወሳኝ ነው። ስለሆነም በሁለተኛው ዕቅድ ዘመን ማጠናቀቂያ የህዝብ እርካታና አመኔታ ደረጃ አሁን ካለበት 60 በመቶ ወደ 85 በመቶ ለማድረስ ግብ መያዙን መረጃዎች ያስረዳሉ።

ለመልካም አስተዳደር መስፈን ዋና መሳሪያ የሆነውን የግልፅነትና ተጠያቂነት ሥርዓት በሁሉም መንግስት ተቋማት ለመዘርጋት በፌዴራልና በክልል የመንግስት ተቋማት የዜጎች ቻርተርን በተሟላ ሁኔታ በመተግበር በተቋማት የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራር የበለጠ እንዲጎለብት የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ።

እነዚህ ስራዎች መልካም አስተዳደርን ሊያስገኙ የሚችሉ ናቸው። አስፈፃሚው አካል አፅመዋለሁ ብሎ ከህዝብ ተወካዩችምክር ቤት ጋር የገባው ውል ይህን ለመፈፀም ያስችላሉ። ስለሆነም ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል።

ስለሆነም ሁሉም የሪፎርም ፕሮግራሞች በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበሩና ለውጡ ስር እንዲሰድና ተቋማዊ ባህል እንዲሆን ብርቱ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። ለዚህ ጥረት ደግሞ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ዜጎች በመንግስት ስራ ውስጥ ድጋፍ ሲያደርጉ ስኬታማ ውጤቶችን ማስመዝገብ ስለሚቻልና ችግሩ እንዲቀረፍ የራሱ ሚና ስላለው፣ ጉዳዩን በትኩረት በመከታተል እገዛ ማድረግ ተገቢ ያስፈልጋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy