Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አራምባ ና ቆቦ ሰለማዊ ሰልፍ በ ፊንፊኔ

0 3,703

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አራምባ ና ቆቦ ሰለማዊ ሰልፍ በ ፊንፊኔ

መስከረም 7/2011

ተስፋዬ ሺ

ሰሞኑን በፊንፊኔና አከባቢዉ የሚከሰቱ ግጭቶችና ጉዳትን ተንተርሰዉ የአዲስ አበባ ልጆች ጉዳዩን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ መዉጣቸዉን አይተናል፡፡

በርግጥ የተከሰተዉ ግጭት ና የደረሰዉ ጉዳት ማንንም የሚያሳዝንና ሁሉም ኢትዮጽያዊ ያወገዘ ድርጊት ነዉ፡፡  ነገር ግን ሰላማዊ ሰልፉ ላይ በጣም የታዘብኳቸዉ ነገሮች አሉ፡፡

በንጹህ አዕምሮ ስንመለከት ጉዳዩን ያለ ማዳላት እናዉራ ከተባለ ሰላማዊ ሰልፎቹ ከ ግጭቱ ባሻገር ለርካሽ ፖሊቲካ ፍጆታ እንዲዉሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን የሚያሳዩ ነገሮች አሉ፡፡

እስቲ የሰላፉ አላማ ያልሆኑ ግን ከግጭቱ በላይ ትኩረት ያገኙ መፈክሮችን እንይአቸዉ

አንደኛዉ “ጀዋር  ሞሃመድ ከ ኢትዮጽያ ይዉጣ !”  ይህ መፈክር እዉነትም የአዲስ አበባ ልጆች በራሳቸዉ ተነሳሽነት ጀዋርን ጠልተዉ ወይም ጀዋር ጥፋትን አጥፍተዉ ያሉት ሳይሆን የከሰሩ ግንቦት ሰባት አባላት በተለይ የጀዋር አመለካከትን የሚቃወሙ ቡድኖች ያዘጋጁት ሴራ መሆኑን ማንም ሊያዉቀዉ ይችላል፡፡

እነኚህ ቡድኖችን ያበሳጫቸዉ ነገር ቢኖሩ ሁለት ናቸዉ አንደኛ  ጀዋር ለ ኦነግ አቀባበል ቅድመ ዝግጅት ለቄሮዎች ያስተላለፈዉ መልዕክት  ነዉ፡፡ እሱም ማንኛዉም ቄሮ ኦነግን ለመቀበል ሲመጣ ልሙጡን ባንዲራ ሳይሆን  የፌዴራል ፤የኦነግ ፤እንዲሁም የሁሉም ክልሎች ባንዲራ ብቻ መሆን አለበት ብሎ  በመናገሩ ነዉ፡፡ የጀዋር መልዕክት እንደዚህ መሆኑ ደግሞ ለነኚህ ለአንድ ዘር አቀንቃኞች ከሞት በላይም ሞት ስለ ሆነባቸዉ  በብር ገዝተዉም ቢሆን ጀዋር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አስወጥተዋል፡፡ ነገር ግን ማወቅ የሚገባን ጀዋር ሞሐመድ እኛ ከምናስበዉ በላይ ለእዉነተኛ ፌዴራሊዝም የሚከራከር አክቲቪስት እንጂ ለርካሽ ፖሊቲካ የሚሯሯጥ እንዲሁም  አንድ ኢትዮጽያ፤ አንድ ቋንቋ፤ ምናምን እያለ የማይሆን ህልም የሚያልም ሰዉ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ሰዉ በኦሮሞ ቄሮዎች ዘንድ እጅግ ተቀባይነት ስላለዉ ከዚህ ሰዉ ጋር መጋጨት ማለት ባለፈዉ መስቀል አደባባይ ላይ አራት ሚሊዮን በላይ ሆኖ ኦነግን ሲደግፍ ቄሮ ጋር እንደ መጋጨት መሆኑን እያወቁ ትርፉ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችልም በዛዉ እያሰቡ መሄድ ጠቃሚ ነዉ፡፡

ከሰልፉ የሰማሁት ሌላኛዉ መፈክር  “ታከለ ኡማ ( የፊንፊኔ ከንቲባ) ይዉረድ “የሚል ነበር ፡፡ ቆይ እስቲ ታከለ ለምን ይወርዳል?  ታከለ ኡማ ማለት ዶ/ር አቢይ ከሚተማመንባቸዉ የለዉጡ አካል ግንባር ቀደም ወጣት ና ባሁኑ ሰዓት የሚገርም ለዉጦችን እያመጣ ያለዉ ባለ ራዕይ ከንቲባ  ነዉ፡፡ እኛ ሰምተን የማናዉቀዉን አሰራር እያመጣ ፤ ደኃ ህብረተ-ሰቦችን ባለ ቤት እያደረገ፤ የተቸገሩትን እየረዳ ያለ መሪ ነዉ እንጂ ስልጣን አግንቻለሁ ብሎ  ወንበሩን እያሞቀ የሚገባ ወጣት አይደለም፡፡ ታዲያ ለምን ይዉረድ ተባለ ብለን ስናስብ በባለፈዉ የኦነግ አቀባበል ላይ በአካል ተገኝተዉ በአፋን ኦሮሞ ንግግር ስላደረገና የንግግሩ ትርጉም ግራ የገባቸዉ  ጭንቀታሞች ታከለም የሰልፉ ሰለባ እንዲሆን ያሴሩት ሴራ ስለ ሆነ ብዙም የሚደንቅ ነገር አይደለም፡፡

ሶስተኛዉ ከሰልፉ አላማ ጋር የማይመሳሰልና አደገኛ የነበረዉ መፈክር “ኦሮሞ ከአዲስ አበባ ይዉጣ” የሚል ነበር እዚህ ላይ እኔ ማለት የሚፈልገዉ ነገር ካለ ኦሮሞ ከፊንፊኔ ከሚወጣ እንደዚህ ያስባላቸዉ የሴጣን መንፈስ ነዉና ከ አዕምሮአቸዉ ይዉጣ የሚል ብቻ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ይህ መፈክር የአንድ ወይም ሁለት ደቂቃ ምኞት ይሆናል እንጂ መቼም የማይታሰብ ስለ ሆነ እዚህ ላይ ትንተና መስጠት አስፈላጊም አይደለም፡፡

ጉዳዩን ስናተቃልል ይህ ሁሉ ልፋት ከቅናትና ከጭንቀት የመነጨ ሩጫ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እዉነትም ለዚች ሃገር የሚያስብ አካል ካለ ቆም ብሎ ቢመለከተዉ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy