የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እየወሰዱ ያለውን የለውጥ እርምጃ አደነቁ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶከትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሀገሪቱ እየወሰዱ ያለውን የለውጥ እርምጃ አድንቀዋል።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤክል ማክሮን ይህንን የተናገሩት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አሊ ሱሌይማን የሾመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡላቸው ጊዜ ነው።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም አምባሳደር አሊ ሱሌይማንን በኤሊሴ ቤተ መንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ወቅትም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አምባሳደር አሊ ሱሌይማንን ያመሰገኑ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥም አድንቀዋል።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አክለውም፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሀገሪቱ እየወሰዱት ያለው የለውጥ እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እያመጧቸው ላሉ ለውጦችም አድናቆታቸውን እንዲያስተላልፉላቸውም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለአምባሳደር አሊ መናገራቸውን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፊታችን ጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም በፈረንሳይ ፓሪስ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ ወደ ፓሪስ የሚያቀኑትም በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገብዣ ነው።
ፕሬዚዳንት ማክሮን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከዚህ ቀደም በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል።
በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ማክሮን አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ለውጦችን ፈረንሳይ የምትደግፍ መሆኗንም ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ማክሮን በወቅቱ ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሰላም በደረሱት ሥምምነት የተሰማቸወን ደስታ መግለፃቸውም ይታወሳል።
በሙለታ መንገሻ