Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለጋሞ የአገር ሽማግሌዎች ተግባር አድናቆታቸውን ገለጹ

0 558

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሰሞኑን በቡራዩ ከተማና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በአርባምንጭ ከተማ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በቁጣ ሊፈፅሙት የነበረውን የሀይል ድርጊት በአካባቢው ባህል መሰረት ለተከላከሉ የአገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚ ዶር አብይ አህመድ አድናቆታቸውን ገለጹ።

ዶክተር አብይ በጅማ ሲካሄድ በሰነበተውና ትናንት (መስከረም 11) በተጠናቀቀው የኦዴፓ 9ኛ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ‹‹ዘጠነኛው የድርጅታችን ጉባኤ በደቡብ ክልል የጋሞ ሽማግሌዎች በቅርቡ ያደረጉትን ገድል በታላቅ አድናቆት ይመለከተዋል” ብለዋል።

የጋሞ ሽማግሌዎች ተግባር ኢትዮጵያ ሽማግሌዎች እንዳሏት፤ ወጣቶች ዛሬም ባህላቸውን እንዳልረሱና ሽማግሌዎችን እንደሚሰሙ ሰውን ከመግደል ማቀፍ የሚሻል መሆኑን ባለመግደል ማሸነፍ መቻሉን ያሳያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የእነሱን አርአያ የሚከተሉ ሌሎች ሽማግሌዎች እንዲፈጠሩ፤ የወጣቶቹን መልስ ተከትሎ ታላቅን የሚያከብር የሚያደንቅ ወጣት እንዲበዛ ጉባኤያችን ለጋሞ ህዝብና ሽማግሌዎች ያለውን አድናቆት ሊገልፅ ይፈልጋል›› ሲሉ ተናግረዋል።

የጋሞ የአገር ሽማግሌዎችን ተግባር የሚያሳየው ቪዲዮ ከዚህ ዜና ጋር አብሮ ቀርቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy