Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መደመር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አንደበት

0 1,352

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

• ክፉን የማይጋራ የለም ባይባልም፤ ክፉን የማይጋራው ከበዛ ግን ክፋት መክኖ ይቀራል። አደገኛው ነገር አንድ ክፉ ሃሳብ ከአንድ ቀና ልቦና ከሌለው ሰው ሲፈልቅና ብዙዎች ሲጋሩት ለጥፋት ይውላል። የሚጋራው ያጣ እንደሆነ ግን እዚያው ግለሰብ ልብ ውስጥ መክኖ ይቀራልና ክፉ ክፉውን የማንጋራ፣ መልካም መልካሙን የምንደምርና የምንደመር እንድንሆን ያስፈልጋል።
• የመደመር ምሥጢር በፍቅር ለይቅርታ ብቻ ይሁን። ለክፋት፣ ለመግደል አንደመርም። የእኛ መደመር ለሌሎች ተስፋ እንጂ ጭንቀት አይሆንም። 
• ብዙዎች የመደመር ፍልስፍናን ከመሠረታዊ የሂሳብ መሪ ቀመር ጋር ያገናኙታል። ይሁንና የእኛ የመደመር መሪ ሃሳብ ከስሌታዊ ንድፈ ሃሳብ በመጠኑ ከፍ አድርገን ልንመለከተው ይገባል። ምክንያቱም በማቲማቲክስ ፕሪንስፕል ቦዲ ማስ ይባላል። መጀመሪያ ቅንፉን ማፍረስ፣ እኛ ግንቡን ማፍረስ ነው። የእኛ የመደመር እሳቤ ከሂሳቡ ስሌት መሠረት የላቀ ነው። በዚህም የእኛ የመጀመሪያ ቅንፍ ሰበራው የጥላቻ ግንብን ማፍረስ ነው።
• መደመር ከተራው የሂሳብ ስሌት የሚልቅበት ዋናው ሃሳብ እኔና አንተ፣ እኔና አንቺ ስንደመር እንደ ሂሳብ ስሌቱ ሁለት አንሆንም። እኛ ነው የምንሆነው።
• የእኛ የመደመር መሪ ሃሳብ የሚቀንሰው በደል፣ ቂም፣ ክፋት፣ ጥላቻ፣ ስንፍና፣ ቀማኛነት፣አገር አለመውደድ፣ ሕዝብን አለማገልገል ይቀነሳሉ። የመቀነሻው መሣሪያ ደግሞ የማስሊያው መሣሪያ ደግሞ ይቅርታ፣ ምህረት፣ ደግነት፣ ፍቅር ይባላሉ።
• የእኛ የመደመር መሪ ሃሳብ ማካፈልም አለው። የምናካፍለው ፍቅር፣በጎ ቃል፣ጥበብ፣ ነዋይ ይሆናል።
• መልካሙን ስናካፍል፣ መልካሙን ስናብቃቃ መከፋፈል ሳይሆን መደመር ይሆንልናል። ክፉ ተግባር ቀንሰን ተባዝተን በጎ በጎውን አካፍለን በአፍሪካ ቀንድ ስንደመር መደመር ለእኔ ሳይሆን፤ ለእኛ ነውና ሁሌም እኛ ከእኔ ይልቃል።
• የምንደመረው ነገን በጋራ ለማነጽ፣ እንግዶቻችንን በፍቅር ለመቀበልና ለማስተናገድ፣ ደካማውን ለማገዝ፣ ያለንን ለማካፈል፣ ተግተን ለመስራት፣ የበደሉንን ይቅር ለማለት፣ በፍቅር ሁሉን ለማሸነፍ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን ከመበላላት መረዳዳት፤ ከመገፋፋት መተቃቀፍ እንዲሆንልን ነው።
• በመደመር ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን እንሰራለን። ሳንደመር ስንቀር ኪሳራው ብዙ ነው።
• መልካችን፣ ፍቅራችን፣ ደግነታችን፣ ጀግንነታችንም አንድ ዓይነት ነው። ነገር ግን የእኛ መደመር ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ስጋት ሳይሆን ተስፋ፤ ጦርነት ሳይሆን ልማት፤ የሚቀንስ ሳይሆን የሚጨምር ነው።
• ጤንነታችን እንዳያመልጠን፣ ዴሞክራሲያችን እንዳያመልጠን፣ ሰላማችን እንዳይወሰድብን ሁላችንም በአንድ ልብ ተደምረን ዘብ ልንቆም ይገባል። ምክንያቱም አንድ ሰው ቤተሰብ አይሆንም፤ አንድ ቤተሰብ ብቻውን ከተማ ሊሆን አይቻለውም። አንድ ቡድንም እንዲሁም ሙሉ አገር ፈጽሞ ሊሆን አይቻለውም። አንድ አገርም ያለ ሌላ አገር ብቻውን አገር ተብሎ ሊጠራ አይቻለውም። ሌላ ድንበር የለምና።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጳጉሜን 4 ቀን 2010 ዓም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy