‹‹ምንም እውነታ የሌለው የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው የተፈጸመብኝ፡፡ይህ ሆን ተብሎ አንገቴን እንድደፋ እና አመራርነቴም ተቀባይነትን እንዳያገኝ የተደረገ ሴራ ነው፡፡››
ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ከሱዳን ወሰን ጋር በተያያዘ ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት =================================== ብዙዎቹ እንዲህ አይነት ቅሬታ ሲመጣ ለምን ግልጽ አላደረገም ምላሽስ ለምን አልሰጠም የሚሉ ሀሳቦችን ሲሰጡ ሰምቻለው፡፡ በዚህ ላይ ግልጽ ማድረጉ ጠቃሚ ነው ብየ አስባለሁ፡፡