Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በቤንሻጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በኦሮሚያ ክልለ አጎራባች ወረዳዎች በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

0 1,158

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በቤንሻጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በኦሮሚያ ክልለ አጎራባች ወረዳዎች በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በቤንሻጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በኦሮሚያ ክልለ አጎራባች ወረዳዎች በተፈጠረ የጸጥታ ችግር በሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥም ከኦነግ ጋር በተደረገው ስምምነት በስሙ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አቶ አዲሱ በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እንዳስነበቡት በኦሮሚያ እና ቤንሻጉል ጉሙዝ የዞን እና የወረዳ አመራሮች በመስከረም 16 ወይይት እንደተደረገ ገልጸው፤ ውይይቱም በቤንሻጉል ጉሙዝ የተካሄደ ሲሆን፥ አላማውም ከዚህ ቀደም በተፈጠረ ችግር ምክንያት በመነሲቡ እና ቂልጡ ከራ ሰፍረው የሚገኙ ከ13 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቻው የሚመለሱበትን መንገድ ማመቻቸት ነበር ብለዋል።

የዚህ ቀጣይ የሆነው ውይይትም በመንዲ ከተማ የሁለቱን ክልል ዞን እና ወረዳ አስተዳዳሪዎች ብሎም የአስተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎችን በማሳተፍ የተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ አዲሱ፥ ውይይቱም ጥሩ ስምምነት ከተደረገ በኋላ ከቤንሻጉል ጉሙዝ የመጡ አመራሮች ወደ ከማሺ ዞን በመጓዝ ላይ እንዳሉ ቢላ በተባለ አካባቢ በኦነግ ስም የታጠቁ ሰራዊቶች ተሽከርካሪው ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ተናግረዋል።

በዚሁ የተኩስ ልውውጥም የከማሺ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 4 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ነው የገለጹት።

ሰዎቹ ሲጓዙባቸው የነበሩ 2 ተሽከርካሪዎችም መቃጠላቸውም ነው የተገለጸው።

ይህ ድርጊት በተሰማ ወቅትም በከማሺ ረብሽ መነሳቱን እና መንገድ መዘጋቱን የገለጹት አቶ አዲሱ በተወሰኑ ቦታዎች ላይም በኦሮሞ እና ጉሙዝ መካከል ግጭት እንደተፈጠረ ተናግረዋል።

በዚህም ከከማሺ ጋር የምትዋሰነው እና በምእራብ ወለጋ ዞን እንማይ በላዶ በተባለች ቀበሌ የሁለት ኦሮሞ ተወላጆች ህወት ሲያልፍ ሁለት መቁሰላቸውንምን ነው የተናገሩት።

በከማሺ የተፈጠረውን ግጭት በመስጋት በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ምስራቅ ወለጋ መሸሻቸውም ተገልጿል።

በከማሺ የተፈጠረው ግጭት ወደ ከፋ ችግር እንዳይሸጋገር የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ የማራጋጋት ስራ እየሰሩ እንደሆነም ተገልጿል።

ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ችግሩን ለመቅረፍ ወደ ታች ወርደው እየሰሩ ነው ያሉት አቶ አዲሱ የተፈናቀሉ ዜጎችም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

በምእራብ ኦሮሚያ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከኦነግ ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት በስሙ የታጠቁ ሰራዊቶች በአስቸኳይ ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

ኪዚህ ባለፈ ታጥቀው በመንቀሳቀስ እና ህገ ወጥ ድርጊት በመፈጸም የህዝቡን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ላይ ህግ የማስከበር ስራ እንደሚሰራም አቶ አዲሱ አረጋ መናገራቸውን ኤፍ.ቢ.ሲ ዘግቧል ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy