የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብደላሂ መሀመድ ጋር በሶስትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በነገው እለት በአስመራ ይወያያሉ፡፡
ዶ/ር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ
—————————————-
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የአሰብና የምፅዋ ወደቦችን ጎብኙ፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የምፅዋን ወደብ በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው የሰላም ጥረት ፍሬ አፍርቶ ውጤት እያሳየ ነው ብለዋል፡፡
ከአዲስ ዓመት በፊት በኤርትራ ለሁለተኛ ጊዜ ጉብኝት ማድረጋቸው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ያለበትን ወዳጅነት እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡
ቀደም ሲል በአሰብ ባደረጉት ጉብኝት ወደቡ የተወሰኑ የማስተካከያ ስራዎች ተደርገውለት በአጭር ጊዜ ወደ ስራ መግባት የሚያስችል ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል፡፡
መቐለ የተባለችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብም ምጽዋ ወደብ ደርሳ የመጀመሪያ ጉዟዋን ወደ ቻይና ታደርጋለች።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን ማምሻውን አስመራ ገብቷል፡፡