የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብደላሂ መሀመድ ጋር በሶስትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በነገው እለት በአስመራ ይወያያሉ፡፡
ዶ/ር አብይ አህመድ አስመራ ገቡ —————————————- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የአሰብና የምፅዋ ወደቦችን ጎብኙ፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የምፅዋን ወደብ በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው የሰላም ጥረት ፍሬ አፍርቶ ውጤት እያሳየ ነው ብለዋል፡፡