NEWS

ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሃመድ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

By Admin

September 28, 2018

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ጨምሮ በአራት ተጠርጣዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቀደ፡፡

የፌደራል መርማሪ ፖሊስ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ በአራት ተጠርጣሪዎች ላይ የ18 ሟቾችን እና የ438 አካል ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች የህክምና ማስረጃ መሰብሰቡንና ዘጠኝ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለችሎቱ አብራርቷል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት የመርማሪ ፖሊስ የተሰጠው ጊዜ የሰራቸው ስራዎች እና ቀሩኝ ያላቸው ምርመራዎች እንዲሁም የተጠርጣሪዎችን አስተያየት አዳምጧል፡፡

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ለመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡ 

FBC