Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአስደማሚ ትህትናቸውና ሳይሰለቹ የህዝብ ችግር በልበ በሰፊነት በማዳመጣቸው ይታወቃሉ፡፡

በአስደማሚ ትህትናቸውና ሳይሰለቹ የህዝብ ችግር በልበ በሰፊነት በማዳመጣቸው ይታወቃሉ፡፡

0 30,543

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ያልተዘመረለት የለውጥ ሰው!

በአስደማሚ ትህትናቸውና ሳይሰለቹ የህዝብ ችግር በልበ በሰፊነት በማዳመጣቸው ይታወቃሉ፡፡

………አቶ ተስፋዪ በልጅጌ …በእድሜያቸው ወጣት ናቸው፡፡ ያውም ከወጣቶች በላይ ለውጥ ማሽተት የሚወዱ ወጣት . ግን ከእድሜያቸው በላይ ብስል ስለመሆናቸው ሁለመናቸው ያሳብቃል፡፡ ወደ አዲስ አበባ በመምጣታቸው በግሌ ደስ ቢለኝም (በእርግጥ በሃገር ደረጃ የመምራት አቅም ስለመኖራቸው፤ በአካዳሚክ እውቀትም በፖለቲካዊ አቅም የሚመሰከርላቸው የስነታሪክና የ ህብረተሰባዊ እድገት እና አመጣጥ በመረዳት በመተንተን ብቁና ልምድ ያላቸው መሪ መሆናቸውን እመሰክራለው) እንደውም በደኢህዴን ከተስፋዪ ጋር ለ30 ደቂቃ ማሳለፍ አንድ መፅሃፍ አንብቦ መጨረስ ነው የሚል ጓደኛዪን አስታውሳለው፡፡ ይሁንና ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች በተለይ ከደቡብ አካባቢ ተስፋዪ የለውጥ ተፃራሪ እንደሆነና የቀን ጅብ ምናምን የሚል ላም ባልዋለበት አይነት ስያሜ ሲሰጡት ማየቴ አሳዝኖኝ ነው ወደዚህ የመጣሁት ፡፡ ይህ ግን በጣም የተሳሳተ ነው ፡፡

እንደውም በሚገርም ሁኔታ እውነታው ፍፁም በተቃራኒ ነው፡፡ ከርቀት መገምገም ለስህተት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ወይኔ ስቀርበው ለካ እንደተባልኩት አይደለም እንደሚሉት አይነት መሆኑ ነው፡፡ እንደኔ ቀርባችሁ ባያችሁ እላለው ለነዚህ ሰዎች…. …(ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ነውና) እንደኔ እንደኔ …..እንደውም ተስፋዪ አሁን የመጣው ለውጥ እውን እንዲሆን ከጀርባ ሆኖ ትልቁን እና ወሳኝ ሚና የተጫወተ ነገር ግን እንደሌሎቹ ሰዎች ብዙ ያተነገረለት ሰው ነው እላለው፡፡

ለምን አንድ ቀላል ምሳሌ ለማቅረብ ያህል ያኔ ቄሮ መላውን ኦሮምያ ተቆጣጥሮ መንገዶች እየተዘጉ ሃገሪቱ ነብስ ግቢ ነብስ ውጪ በነበረችበት ወቅት ተስፋዪ የወቅቱን ሁኔታ ቀድሞ በመገንዘብ ገና በየትኛውም ድርጅት ስለለውጡ የተለየ ሃሳብ እንኳን በሌለበት የካቲት ወር ላይ አንድ ሰነድ አዘጋጅቶ ለደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቅርቦ ነበር፡፡

(ተስፋዪ ካለመዋሸት የትኛውም የደኢህዴን መዋቅር በሚመሰክረው ባለፉት 10 ዓመታት ያለእረፍት መላው ደቡብና ለሃገሪቱም ጭምር የሚጠቅሙ አንዳንዶቹም በምርምር ሰነድነት የሚያግዙ ሰነዶችን አትረፍርፎ አበርክቷል) ፡፡ በሰነዱም ላይ አሁን ያለው ሁኔታ ሊቀየር የሚችለው በተለይም ዋናው አመራር ሃላፊነት ወስዶ ስልጣን ሲለቅ እንደሆነ፤ እንዲሁም አዲስ አመራር (በግልፅ) ከኦሮሞ ህዝብ (ከኦህዴድ) ወደፊት እንዲመጣ ሲደረግ ብቻ መሆኑን በድፍረት አስቀምጦ ነበር፡፡ ልብ በሉ ማንም ሳይል በፊት……… ያን ጊዜ አንዳንዶች ጉዳዪን በሰፊው አራክሰውታል፡፡

ሆኖም ሃሳቡ በሂደት ትክክለኛ ሃሳብ መሆኑን እኔን ጨምሮ ሌሎችም ተረድተነዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አሰያየም ዙርያ በነበሩ ሂደቶች አቶ ተስፋዪ በይፋ ገና ከመነሻው ማናችንም ከደኢህዴን እጩ ሆነን አንቀርብም! የሚለው ሃሳብ በማራመድ በወቅቱ ጥቂቶችን በእጅጉ ያበሳጨ ቢሆንም ሃሳቡ ግን ድጋፍ በማግኘቱ አጠቃላይ በደኢህዴን ስራ አስፈፃሚም ሆነ በደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ የጋራ አቋም እንዲወሰድበት አድርጓል፡፡

ደኢህዴንም እጩ ላለማቅረብ ማንም ራሱን እጩ አድርጎ እንዳያቀርብ ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ ሆኖም የሆነው ግን የተደረሰውን ስምምነት መሰረት ያደረገ አልነበረም…ስለሆነም …በምርጫ ሂደቱ በነበሩት ወሳኝ ሰአታት ሁኔታውን ለመቀየር የተስፋዪ በልጅጌ ሚና በእጅጉ ከፍ ያለ ነበር፡፡ ምናልባት ያ ትግል አሁንም ድረስ ዋጋ እያስከፈለው እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ከቀኑ 11 ሰአት ከ 17 ደቂቃ ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ተኩል ድረስ የመጨረሻው ተጠቋሚ የአሁኑ መሪያችን ዶ/ር አብይ ተጠቁመው በቀረቡበት ሰአት ያው ጥቆማው በትግል እየፀደቀ እንዲሄድ በተመጠው አቅጣጫ መሰረት በኢህአዴግ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ20 ያላነሱ ተቃውሞዎችና ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል፡፡ ኢህአዴግ አይደለህም ከሚል ሃሳብ ጀምሮ ለአንድ ህዝብ ጥላቻ አለህ እስከሚሉ ተራ ትንቅንቆች ውስጥ ሁሉ ተገብቶ ነበር፡፡

የሆኖ ሆኖ ዶ/ር አብይ እጩ ሆነው እንዲፀድቁ የትግል ጓዳቸው የለማ መገርሳ ሚና ዋናውና ወሳኙ ቢሆንም የአቶ ተስፋዪ በልጅጌና የብአዴን ጓዶች ሚና ቀላል አልነበረም፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያምም በሰአቱ በእኔ ይብቃ …እኔ ላይ ስታደርጉ የነበረው ስም ማጥፋት በነዚህ ወጣቶች ላይ እንድታደርጉ አልፈቅድም በሚል አምርረው በመናገር የአሁኑን ጠቅላያችንን ተከላክለዋል፡፡ በስተመጨረሻም እጩነታቸው ፀድቆ ወደ ድምፅ መስጠቱ ከመሄዳቸው በፊት በነበረችው አጭር እረፍት ብዙ ወሳኝ ስራዎች በተሰሩበት ሰአት ተስፋዪ የደኢህዴን ሰዎችን በመሰብሰብ አሁንም ቢሆን ድምፃችንን ለዶ/ር አብይ መስጠት አለብን በማለት የመጨረሻውን ትግል አድርገዋል፡፡

እነሆም ያው ድምፁን ማን ማን ሰጠ የሚለው በትክክል መናገር ባይቻልም፤ አንዳንዶች ምኞታቸው ከንቱ ሆኖ እንዲቀር ሆኗል፡፡ እነሆ ዶ/ር አብይም ሃይለማርያም ከአንድ ምርጫ ዘመን በፊት ካገኘው 98 ድምፅ የተሻለ ድምፅ ጭምር አግኝተው የሊቀመንበርነቱን ቦታ ተቆናጠጡ፤ ብዙዎችም በተሳሳተ ስሌት የነጎዱ ከፍተኛ ድንጋጤ ዋጣቸው፡፡ እናም የዚህ ሂደት ውጤት አንዳንዶችን የለውጥ አምጪ ቁንጮ አድርጎ ሲሰቅላቸው ተናጋሪ የሌላቸውንና በስራ ብቻ ለሚያምኑት ለእንደነተስፋዪ አይነቱ ሰው ተጨማሪ ስም የሚያሰጥ ሆኖ መመስገኑ ቢቀር እንኳን ለረጅም ጊዜ ያንን አስቸጋሪ እና ሰፊ አይነት ጥያቄ ያሉበት ክልል በአግባቡ አቻችለው ሲመሩ የቆዪት አቶ ተስፋዪ የጥቃት እና የቂም መወጣጫ አይነት በሃሰተኛ ስም ማጥፋት ቅንብር ሰለባ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡

ይሄንን እያየሁ መቋቋም ስላልቻልኩ ይህችን ፅሁፍ ጀባ አልኩ በአዋሳ ተጀምሮ በሁሉም ቦታ በተቀጣጠለው የአመፅ ድርጊት ሁሉም የአቅሙን ያህል ቢያደርግም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ የማይካድ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህም ችግር ቢሆን የአቶ ተስፋዪን ጀግንነት የሚሸፍነው ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን ተስፋዪ ማንም ቢሆን በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ መቆጣጠር የሚችልበት እድል አልነበረውም፡፡ ከስሜት ወጥተን በምክንያታዊነት ካሰብን ደኢህዴን የአገራዊ አንድነቱ ዋልታ ሆኖ እንዲወጣ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ እኚህ በለውጥ በእጅጉ የሚያምኑ መሪ ባለፉት አመታት ለደቡብ ክልል ለውጥ ከማንም በላይ መልፋታቸውን ሊክድ የሚችል የለም፡፡ ሌት ተቀን ያለእረፍት የለፉለት የደቡብ ክልል ለሁሉም አካል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሰላሙ ደፍርሶ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሃል ጥቂቶች እሳቸውም ላይ እጃቸውን ለመቀሰር ሲሞክሩም አስተውለናል፡፡

ይህ ግን በእውነቱ ፍፁም የግለሰቡን ማንነት የማይወክል ሃሳብ ነውና ለሚገባው የሚገባውን ብንሰጥ የሚል አሳብ አለኝ፡

አልማዝ ድልሰቦ አዋሳ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy