Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትሰራለች” ፕሮፌሰር አፈወርቅ

0 1,071

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በዛሬው ዕለት ( መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም ) ከካናዳ አምባሳደር አንቶይን ቼርቬር የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ተቀብለዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያና ካናዳ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመጠቆም አሁን ባለው የለውጥ ግስጋሴ ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር መንግስት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡ ለዚህም በየአመቱ የሚካሄደው የሁለትዮሽ የፖለቲካ የምክክር መድረክ ጠቃሚ መሆኑንም አስምረውበታል፡፡

በካናዳ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው የሁለቱን አገሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳለጥ ግንኙነታቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው፣ ኢትዮጵያ ከድህነት እንድትወጣ በካናዳ በኩል ለሚደረገው ያልተቋረጠ የልማት ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለውም ኢትዮጵያ፣ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ተግባራት ማከናወኗን አስረድተዋል፡፡ ከጎረቤት አገራት ጋር ያለው የኢኮኖሚ ትስስር እንዲጠናከር ሰፊ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ክቡር አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሁለቱን አገሮች ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ለሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጎናቸው የማይለይ መሆኑን በመጠቆም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

አምባሳደር አንቶይን ቼርቬር በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለችበት ወቅት አምባሳደር ሆነው መመደባቸው ያስደሰታቸው መሆኑንና ይህም ለስራቸው ጉልበት እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡

በካናዳ ያለው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አምስት ጊዜ ወደ ካናዳ መብረሩ የሁለቱን አገሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን አምባሳደር አንቶይን ቼርቬር ገልጸዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy