ከኢህአዴግ ጉባኤ ከሚጠበቀው ከመሰረታዊ ሀገራዊ አጀንዳ ይልቅ በኃላፊነት መተካካት የስብዕት ማዕከልነን የሳበው የማህበራዊ ሚዲያ ትኩርት ያገኘው ዘመቻ ሰሞነኛ ትዝብት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይኽውም የግንባሩ ሊቀመናበርት ምርጫ ነው ፡፡
ምክንያቱም የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር ተነስተው በሙፊሪያት ካሚል ተተክተዋል የሚለው ውስጥ አዋቂ መሰል አሉባልታ ተጠናክሯል፡፡ እውነታውን ከኢህአዴግ 11ኛው መደበኛ ጉባኤ መጠናቀቅ በኃላ የምናውቅ ቢሆንም አሉባልታው ትክክል ከሆነ ግን ታሪካዊ ስህተትና ክህደትም ጭምር ነው፡፡ክህደቶም ኢህአዴጋዊ ክህደት ነው፡፡
ምክንያቱም፦
1ኛ/ በሀገሪቱ በታሪክም ሆነ በባህል እንዲሁም በቁጥር ጭምር ትልቅ የሆነውን የአማራን ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዳይሆን አግላይ ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ ፤በነገራችን ላይ አንዳንድ ሰዎች አማራ የሚለው ብሔር ሲነሳ ለምን የብሔር ጥያቂ ታነሳላችሁ ይላሉ፡፡ ይህ አባባላቸው እጅግ በጣም ያስቀኛል፡፡ምክንቱም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን ያላገናዘብ እና ዶክተር አብይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመረጥ የመጀመሪ የፓርላማ ንግግሩን ከማድረጉ በፊት እኮ በብቃቱ ሳይሆን ሳናውቀው ኦሮሞ በመሆኑ ነው የኢህአዴግ ሊቀመንበር እንዲሆን የተደረገው፡፡ መቺም ይህ ጥሬ ሀቅ የሚካድ አይመስለኝም፡፡
በኃላ ግን ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ወሳኔን ተከትሎ የመፈፅም እና የማስፈፅም ብቃቱን ያየነው በኃላ ነው ፡፡ በእርግጥ ዛሬ ላይ የጓድ ዶክተር አብይ አህመድ ብቃት የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ይሁን እንጂ የመጅመሪያ ምርጫ ግን ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ሰለዚህ አማራ ተገቢውን ቦታ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማግኘት አለብት ስንል በምክንያታዊነት ነው፡፡
2ኛ/ጓድ ደመቀ መኮንን የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ የመምራት በእሳት የተፈተነ አቅም ያላቸው በመሆኑ ለቦታው አሁን ከአሉት የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ሊቀመናበርት መካከል በአቅም ሲመዘኑ ለምክትልነት እጅግ በጣም ከበቂ በላይ ነው፡፡
3ኛ/ በ12ኛው የአዴፓ ድርጅታዊ ጉባኤ የተሰጡ የወሰን፣የማንነት፣የድንበርና የኢኮኖሚ ጥያቂ ለመፈፅም የገቡትን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ መነሳሳትናቆጭት ውስጥ ናቸው፡፡
በተለይም ባለፎት 20 ዓመታት ከነበረው የሲራ ፖለቲካ አጉበር ተላቀው በሙሉ አቅም በሚገኙበት ወርቃማ ጊዜ ቦታው እጅግ በጣም ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ቦታ ለአማራው ተወካይ ለጓድ ደመቀ መኮንን ነው፡
ድልና ድምቀት ለኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ!!!