Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ካናዳ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እያደረገች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አደነቀች

0 1,367

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ካናዳ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እያደረገች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አደነቀች

/የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያደረገቸው እርቀ-ሰላም እንዲሁም በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገው ጥረት ለክልሉ ሰላምና ልማት ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተገለጸ፡፡

በካናዳ ኦታዋ በተካሄደው የ7ኛው የኢትዮ-ካናዳ የምክክር መድረክ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ነቢያት ጌታቸው የተመራው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በካናዳ የአለም ዓቀፍ ጉዳዮች ከሳህራ በታች አገሮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ማርክ አንድሬ ፍሬዴቴ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ምክክር አድርጓል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከካናዳ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኢያን ሽጋርት ጋር በሁለቱ አገሮች የጋራ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡

ኢያን ሽጋርት በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የለውጥ ሂደት በማድነቅ ለዚህም የካናዳ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ የልዑካን ቡድኖች ትስስሩን የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያጎለብቱ ትብብሮች እንዲሁም በአካባቢያዊ እና በአለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይም ጭምር ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል፡፡

ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ማርክ አንድሬ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ የህዝቡንና የመንግስትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡
የሴት ካቢኔ ቁጥሩን ከወንዶች ጋር እኩል መደረጉ እንዲሁም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የተደረገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመጠቆም፣ ለውጡ ተቋማዊ እንዲሆን የካናዳ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም ማርክ አንድሬ አውስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በግብርናና በኢንዱስትሪ ልማት ለምታደርገው አበረታች እንቅስቃሴ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ላይ ለሚደረገው ጥረት የካናዳ መንግስት ድጋፉን እንደሚቀጥል በልዑካን ቡድኑ ተወስቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፤ የቀረጥ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ በማድረግ የኢትዮጵያን የወጭ ንግድ ዘርፍ ለማጠናከር እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ለማድረግ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በመጨረሻም ለሁለት ቀናት ያክል የተካሄደው የምክክር መድረክ የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች በማጠናከር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሩን የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy