CURRENT

ወልቃይት ጠገዴ በትግራይ ክልል ውሥጥ የገባው ዛሬ አይደለም

By Admin

October 29, 2018

ወልቃይት ጠገዴ በትግራይ ክልል ውሥጥ የገባው ዛሬ አይደለም፣ ከ 27 ዓመታት በፊት ነው። ራያ ትግራይ የሆነው በአብይ አይደለም በመለስ ነው።

ከሞት ባይኖር ሲደልል

አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ተደርጎ ሲሳል፣ አማራው የኦሮሞው ገዳይ ሲባል፣ አማራው የኤርትራ ሕዝብ ጠላት ሲባል አማራው የት ነበር? ባላጠፋው ስወነጀል ምነው አማራው አልፎከረ? ዛሬ ግን በገሀድ “ በአፈሙዝ መብቴን አስከብራለሁ” ያለው በፍቅር እንኑር የሚል ሲመጣ ነው። መለስ ዜናዊን ለ20 ዓመታት የረባ ተቃውሞ ያላደረገ አማራ፣ ዛሬ መሣሪያ አነሳለሁ አትንኩኝ ብሎ ወጣ። ለመሆኑ መብታችንን በኃይል የምናስመልሰው ዛሬ ነው? ያኔ መብታችን በኃይል ሲወሰድ ኃይላችን የት ነበር? መለስ ከመሞቱ በፊት በኃይል ተነጠቅን የምንለውን ጠገዴን ለምን አላስመለስንም? የዛሬው የጎንደር ጥያቄው ብቻ አግባብ ሊሆን ይችላል። በተቃውሞ፣ በኃይል፣ በአፈሙዝ፣ የሚሉት አባብሎች ግን ተገቢ አይድደሉም። እንኳን እንደ አብይ አይነት በፍቅር እንኑር የሚለው ቀርቶ፣ የተለካ ድሞክራሲ ለሰጠን መለስ ዜናዊን እንኳን በኃይል ሳይሆን በኃሳብ ማሸነፍ ያለብን ዘመን ላይ ነን። አማራው በኢትዮጵያ ጥላ ስር እንጂ በአማራ ብሔር ስር ሲሰባሰብ አዘንኩ። ትውልዴ ከጎንደር ወጣ ብላ የምትገኘው ሸንበቂት ቢሆንም በአማራ ስር አልደራጅም። አማራ ወይንም ሞት ከሚሉጋ ሕብረት የለኝም። ዛሬ ወልቃይት የኢትጵያዊ ሁሉ እንጂ ወልቃይት አማራም ትግራይም አይደለም ብዬ ማሰብ ነው የምፈልገው። ጠገዴ የትግራይ፣ ጠገዴ የከንባታ፣ ጠገዴ የኦሮሞ፣ ጠገዴ የኔም የሁላችን ነው። በመንደር እና በብሔር አልደራጅም። ድርጅቴ ኢትዮጵያ፣ ማኅበሬ ኢትዮጵያ፣ ብሔሬ ኢትይጵያ ናት፡