NEWS

የአገሪቱ የወጪ ገቢ ንግድ በጥቂት ግለሰቦች መያዙን ጥናት አመለከተ

By Admin

October 23, 2018

በቤተሰብ የተያዙ 5 ወይም 6 የሚሆኑ የንግድ ተቋማት አጠቃላይ የአገሪቱን የወጪ ገቢ ንግድ እንደሚቆጣጠሩት የፌደራል እምባ ጠባቂ ተቋም ያሰራው ጥናት አመለከተ᎓᎓

የፌደራል እምባ ጠባቂ ተቋም በአዲስ አበባ በሸማቾች ላይ የሚደርሰውን የዋጋ ንረት በተመለከተ ባስጠናው ጥናት ላይ በቢሾፍቱ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡