Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቅንጅት የፈረሰበትን ምክንያት ለመናገር እንደማይፈልጉ ወ/ት ብርቱካን አስታወቁ

1 2,888

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ቅንጅት የፈረሰበትን ምክንያት ለመናገር እንደማይፈልጉ ወ/ት ብርቱካን አስታወቁ

የቀድሞው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራር የነበሩት ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ቅንጅት የፈረሰበትን ትክክልኛ ምክንያት ለመናገር አልፈልግም አሉ።

ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በሁዋላ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ወ/ት ብርቱካን፤ “ቅንጅት የፈረሰበት ትክክለኛ ምክንያት ምንድን ነበር?” ተበለው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፤ “እውነት ለመናገር አሁን ይሄንን ጥያቄ ልመልስ አልፈልግም፡፡ ልመልስ የማልፈልገው መልስ ስለሌለኝ ወይም ደግሞ ምክንያቱን ስላማላውቀውና ስለማልችል አይደለም” በማለት ምክንያቱን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ወ/ት ብርቱካን አያይዘውም፤ “እስካሁንም የተነሱትን ነገሮች ሚዲያ ላይ አይቻለሁ፡፡ አሁን አገራችን ከሁላችንም አፋጣኝ ምላሽ የምትፈልግበት ወቅት ነው፤ ከዚያ ይልቅ ሌሎች በጣም አንገብጋቢ ጥያቄዎች አሉ” በማለት የግል አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል።

ከዚህ በፊት በነበረን ነገር ማን ጥፋተኛ ነው ፤ ማን የበላይ ነው? ማን የበታች ነው? ማንነው ያፈረስው? ለምን ፈረሰ? የሚለውን ነገር የአካዳሚክ ጥናት ለሚያደርጉ ሰዎች በጣም ጥሩ የጥናት መስክ ሊሆን ይችላል ያሉት ወ/ት ብርቱካን “አሁን እኔ በዚያ ንትርክ ላይ የመሰማራት ፍላጎት የለኝም፡፡ ለህብረተሰባችንም ዋና ጉዳይ ነው ብዬ አልወስደውም” ሲሉ ገልጸዋል።

ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ በሰኞ ህዳር 3 ቀን 2011 ዓም እትም ላይ ይጠብቁ
በማህሌት አብዱል

  1. Mulugeta Andargie says

    ብርቱ! ብርቱ! ብርቱካን
    መለስ ኣፍጥጦ፤ እንደ ሰይጣን
    ቅንጅት እያልሽ፤ ሆነሽ ዲያቆን
    ጴጥሮስ ሶስቴ እንደከዳው ሳይሆን
    ብቻ! ብቻ! ብቻ! ግራ መጋባትን
    የጌታን ወንበር ሲመኝ፤ መራገም ሆኖ ዲያብሎስን
    ሳስታውሰው ያን ትዝታን
    ለቀበሌሽ ተመኝተሽ፤ ሙገሳን
    እንዲያው፤ እንዲያው፤ ምኑ ታይቶሽ ነው? ብርቱካን??
    ቅንጅትማ ፈረሰ! የጌታን ወንበር፤ ተመኘ!ወረፈን!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy