የትናንት ማታውን የፕሮፌሰር ብርሀኑ የ ኢቲቪ ሃርድ ቶክ ፕሮግራም ተመለከትኩት
ፕሮፌሰር ብርሃኑ 1997 ላይ አዲስ አበባን ተረከቡ ተብለን እምቢ አላልንም! ብለዋል ልንረከብ ሄደን ኢህአዴግ እምቢ ብሏል ዞርበሉ ነው የተባልነው! በማለት ተናግረዋል!(????????)
ጋዜጠኛውን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ በሳል ነበር …ተራ ክርክር ውስጥ አይገባም፤ ግን ደግሞ ጥያቄውን በደንብ ኮንስትራክት አድርጎ ዳኝነቱን ለህዝብ ይተወዋል፡፡ በቃ ይሄ ምርጥ አካሄድ ነው፡፡
ፕሮፌሰሩ ብዙ አሪፍ ቁም ነገሮችን ተናግረዋል፡፡ በኢቢሲ መቅረባቸውም የፈጠረባቸው ነገር ያለ ይመስላል፡፡ እውነትም ለሃገሪቱ የዲሞክራሲ ግንበታ አንድ ተጨማሪ ከፍታ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ፕሮፌሰሩ መቼም ቢሆን የማይሻገሯቸው የሚከተሉት እውነቶች ላይ ግን ማለፍ ሳይችሉ መቅረታቸውን ግን በግልፅ ታይቷል፡፡
1. የሰራዊታቸው ጉዳይ ነው፡፡ ያው እንደሚታወቀው አ/ግ 7 በርካታ ሃበት ከአሜሪካና ከመላው አውሮፓ ሲያሰባስብና እየተዋጋሁ ነው በርካታ ሰራዊት በትጥቅ ትግል ላይ ነው ሲሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እናም ጋዜጠኛው ሁለት አንጓ ጥያቄዎችን ጠይቋቸዋል፡፡ አንደኛው የነበራችሁ ሰራዊት ከመንግስት ጋር እውነት ተዋግቶ ያውቃልን??…… ያስቃል ራሱ ጥያቄው…በውጪ አለማት ላይ ያለው የእውነት መለያ ሳይንሳዊ ወንበር ቢሆን ይሄኔ ጩኽቱን አቅልጦት ነበር፡፡..ከእሳቸው በስተቀር ይሄንን ጥያቄ ማንም ደፍሮ እንደማይመልሰው ሁሉም ያውቀዋል፡፡ መልሱን ሲመልሱ ትንሽ አላባቸው….ግራ የተጋቡም መሰሉ… ጋዜጠኛው እዚሁ ጥያቄ ላይ አከለ፡፡ የፓርቲያችሁ ዋና ፀሃፊ እኮ አቶ አንዳርጋቸው፡፡ አንድም ውጊያ አድርገን አናውቅም ብሎ ተናግሯል፡፡ ….ይሄኔ ፈጠን ብለው ፕሮፌሰሩ …እሱ እኮ ታስሮ ነበር ያኔ!…አሉ….የፀሃፊውን ጉዳይ በዚህ ዘጉ ….ግን እኮ እኚህ ሰው ከተፈቱ በኋላ ነው ይሄንን ያሉት ያውም የፓርቲውን መረጃዎች በሚገባ ማግኘት በሚችሉበት ሁኔታ…. ቀጠሉ ፕሮፌሰሩ …መንግስት ራሱ እኮ እንደተዋጋን አምኗል አሉ፡፡ …ገራሚ ነው መንግስት የት እና እንዴት እንዳመነ በግሌ ባላውቅም…..በዛም ሆነ በዚህ ስለተዋጋ ሰራዊት በ21ኛው ክ/ዘመን በዚህ ዲጂታል ዘመን ብዙ ማስረጃማቅረብ በተቻለ፡፡ አርበኞች ውጊያ ላይ እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ ግን ማቅረብ አልተቻለም፡፡
ሁለተኛው እዚሁ ጥያቄ ላይ የሰራዊቱ ቁጥር ነው፡፡ አንዳርጋቸው በተናገረው መሰረት የሰራዊቱ ቁጥር ከ5ሺህ በላይ ነበር በኤርትራ የገቡት ግን 300 ናቸው የሚል ግልፅ ያለ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ ብርሽ ለዚህም ጥያቄ አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው 300ው ነው እንጂ በኤርትራ ከ4ሺህ በላይ ሰራዊታችን በሃገር ውስጥ ነበር ያለው አሉ፡፡ አሁን ይሄንን ማን ያምናል፡፡ አገር ውስጥ የት??…መቼም አንድ ላይ ተሰብስበው በአንድ ካምፕ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ስለዲሞቢላይዜሽን ሲናገሩ እናንተን ካምፕ አናስገባም አሉን በያላችሁበት ዲሞቢላይዝ ሁኑ ብለውናል ብለው የማይታየው ሰራዊት ሳይታይ ወደየቤቱ ገባ የሚል ድራማ የሰሩብን፡፡ አንድ ትጥቅ ትግል ላይ ነኝ የሚል ድርጅት ከ90 በመቶ የማያንስ ሰራዊት ነኝ ተብዬ በየቤቱ ከእናቱ ጋር ተኝቶ 10 በመቶ በጫካ ውስጥ ነበር አይነት ተረት ተረት ማንንም አያሳምንም፡፡ (ለዶላሩ እንደሆነ አፉ ብለንሃል ብርሽ)
2. ሁለተኛው ቁልፍ ጥያቄ የነበረው የትኛውምን ትግል ተከትለንም ቢሆን (ለምሳሌ የመሰረተ ልማት ላይ ቢሆን ጉዳት እናደርሳለን) ብላችሁ ተናግራችኋል ብሎ አፋጠጠው፡፡ መሰረተ ልማት እኮ መንግስትም ቢቀያየር የህዝብ ጥቅምና የሃገር ሃብት ነው ብሎ እንቅ አደረገልኛ…….. ብርሽ እዚህ ጋር ዘባረቀች……አንዴ ይሄ ምኑ ነው ስህተቱ.??.ብላ ጋዜጠኛውን ልታፋጥጥ ስትሞክር ቆየችና……ጋዜጠኛው ሲሪየስ ሆኖ እንዴ ይሄ እኮ የህዝብ ሃብት ነው፡፡ የሚጎዳውም ህዝብ ነው እያለ ሲናገር …ብርሽ መሪውን ጠመዘዘችውና እኛ እኮ የኢኮኖሚ ጉዳት ያልነው የዶላር ማእቀብ እንዲደረግ ብቻ ነው…ብሎ እርፍ……ኸረ አይነፋም…እኛ ሁላችን የሰማነውን ….
3. የህዳሴ ግድብ በተመለከተ በዚህ የባንዲራ ህዝብ ፕሮጀክት ተገቢ ያሆነ ልዪነት ነበራችሁ ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ህዳሴ ግድቡ በአንድ ቀን እኮ ነው አቶ መለስ ካልተሰራ ብለው የግድቡ መሃንዲ ምናምን የሚል ስም ለማግኘት ተብሎ እያሉ ፕሮፌሰሩ ዋናውን አጀንዳ ትተውት ሊያመልጡ ሞክረዋል፡፡ በእርግጥም በአንድ ቀንም ይታሰብ በአንድ ሰከንድ …የግድቡ ጠቃሚነትና ሃገራዊ ምልክትነት ላይ ግን የነበራቸው ልዪነት ሊያሳየዪን አልቻሉም፡፡ ውሃ የማይቋጥር ነበር….. ሌሎችም በርካታ ሃሳቦች ለሙግት የሚያጋልጡ ነበሩ…
በአጠቃላይ በቃለምልልሱ ከሞላ ጎደል ጥሩ ነበር፡፡ እሳቸውም ላይ ለውጡን ከመደገፍ አንፃር ያሳዪት አስተማሪ መልእክቶች ግን ለሌሎች ፓርቲዎችም ጭምር አስተማሪ መሆኑ መካድ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን አ/ግ/7 ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ታይተውበታል፡፡
Prev Post
Leave A Reply
Cancel Reply This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos
ሰዎች!! ብርሃኑ ነጋ ቦንገርና ኣንዳርጋቸው ጽጌ ሸፍተው የነበሩት፤ ያባታቸውን ሃብት (መሬት)ለማስመለስ ነበር። ያውም እኮ ከኦሮሞ ክልል ነበር። ስለዚህ የራሳቸው ታርጌት ነበራቸው። ምን ብለህ ከነዚህ ጋር ትወያያለህ? ብትል ብትል ብትል ብትል ኣይሰሙህም። ውይይቱ ኣፍ ሟሞጥሞጥ ካልሆነ በቀር። የብርሃኑ ነጋ ቦንገር ኣባት፤ ማለትም፤ ኣቶ ነጋ ቦንገር በጅማ ውስጥ ኣንዱን እውራጃ እንዳለ የቡና መሬት ኣርገውት ነበር። ቦንጋ ኣውራጃ ነው። ከኔ ኣባት ጋር የቅርብ ወዳጅነት ነበራቸው።