Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ካቅማቸው በላይ ታክስ የተጠላባቸው ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች እዳ ተሠረዘ

0 768

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

ንቅናቅው “ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!” በሚል መርህ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በንቅናቅው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ እንጅነር ታከለ ኡማ የከተማ አቀፍ የታክስ ንቅናቄው በዋነኛነት ለግብር ከፋዩ ከብልሹ ምግባር የፀዳ የስራ አካባቢን በመፍጠር እና ለአዲስ አበባ በከፍታዋ ልክ የታክስ አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የከተማው ግብር ከፋይ መክፈል ያለበትን ብቻ እንዲከፍል እና መንግስትም የሚገባውን ብቻ እንዲያገኝ የሚረዳ” መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አንገታችንን ያስደፋንን ድህነት ለመዋጋትም ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችን ሊጠናከር ይገባል ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

ከግብር አሰባሰብ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የታክስ ማሻሻያ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በ2003 እስከ 2010 ዓመተ ምህረት በነበረ የግብር ትመና ካቅማቸው በላይ ታክስ የተጠላባቸው ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች እንዳ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ውሳኔ የተላለፈባቸው እና በሂደት ላይ የሚገኙ 1 ሺህ 780 ነጋዴዎችም እዳቸው እንዲሰረዝ እና ክሱ እንዲቋረጥ ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ከግብር ትመና ጋር በተያያዘም ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግብር ከፋይ መብቱን የሚያስከብርበት የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን እንደ አዲስ መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡

የከተማ አቀፍ የታክስ ንቅናቄው በዋነኛነት ለግብር ከፋዩ ከብልሹ ምግባር የፀዳ የስራ አከባቢን በመፍጠር እና ለአዲስ አበባ በከፍታዋ ልክ የታክስ አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የከተማው ግብር ከፋይ መክፈል ያለበትን ብቻ እንዲከፍል እና መንግስትም የሚገባውን ብቻ እንዲያገኝ የሚረዳ” መሆኑን በማንሳት ሰፊ ማብራርያ አድርገዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 19 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 18 ነጥብ መሰብሰብ እንደተቻለ ተነግሯል፡፡

መድረኩ የታክስ ንቅናቄው ትግበራ የሚበሰርበት እና የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ለመወጣት ቃል የሚገቡበት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩ ላይ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy