NEWS

ስልጣን የሚያዘውም፣ ስልጣን ላይ መቆየት የሚቻለውም ህዝብ ሲፈቅድ ብቻ ነው፤ – አቶ ታዬ ደንደኣ

By Admin

January 09, 2019

ኣንኛውም ፓርቲ ስልጣን መያዝ የሚችልውም ሆነ ስልጣን ላይ መቆየት የሚችለው ህዝብ ሲፈቅድ ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ መንቀሳቀስ እንደሚገባ የኦሮሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዬ ደንደኣ አሳሰቡ፡፡

አቶ ታዬ፣ በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሰላም ሁኔታ አስመልክቶ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ማንኛውም ፓርቲ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን አምኖ መቀበል ይኖርበታል፡፡አማንኛውምባለፈም የትኛውም ፓርቲ ወይም ድርጅት ስልጣን መያዝም ሆነ ስልጣን ላይ መቆየት የሚችለው ህዝብ ሲፈቅድ ብቻ ነው፡፡

በመሆኑም በክልሉ ባልተገባ መልኩ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገው ተግባር የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት በተረዳ መልኩ መቃኘት፤ የህዝቡንም የሰላም ፍላጎት ማክበር ይኖርበታል፡፡

እንደ አቶ ታየ ገለጻ፤ ለውጡን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል በርካታ ፓርቲዎች ወደ አገር ውስጥ ከብተው የለውጡ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልልም በተመሳሳይ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ መልኩ ሕግን አክብረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኦነግ ሸኔ የተባለው ፓርቲ ህዝብን በማደናገርና የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ባቋራጭ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በክልሉ ለሰላም መደፍረስ ምክንያት ሆኗል፡፡

መንግስት እስካሁን ችግሩን ለማቃለል በርካታ የሰላም አማራጮችን ቢከተልም ፓርቲው ለመታረም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ እናም አሁን ላይ መንግስት ማድረግ የሚችለው ሕግን ማስከበር ነው፡፡ የህዝቡ ፍላጎትም ይሄው ነው፡፡

እናም ክልሉን የሚመራውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ ህዝቡ ሲፈቅድ ብቻ ስልጣን ላይ መውጣት እንደሚችል እና ሕዝቡ እስከፈቀደ ብቻም ስልጣን ላይ መቆየት እንደሚችል ተገንዝቦ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡ የክልሉ መንግስትም የህዝቡን የስልጣና ባለቤትነት ለማስጠበቅ የክልሉን ሰላም የማስፈን ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በወንድወሰን ሽመልስ