Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተመራ የልኡካን ቡድን ወደ ጅቡቲ አቀና

0 733

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ቡድን ዛሬ ወደ ጅቡቲ አቀና።

የልዑካን ቡድኑ ወደ ሥፍራው ያቀናው በ15ኛው የኢትዮ-ጂቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለመሳተፍ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ገልጿል።

የልኡካን ቡድኑ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት የተውጣጡ ከ10 በላይ ሚኒስትሮችንና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ያከተተ ነው ተብሏል።

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪና የገቢ ንግድ መስመር ሆኖ ያገለገለው የጂቡቲ ወደብ የአገራቱን ግንኙነት ጥንካሬ ማሳያ ነው ተብሏል።

ሁለቱ አገሮች በመሰረተ ልማት የተሳሰሩ ከመሆናቸውም በላይ የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ግንኙነታቸውን በየጊዜው እየገመገሙ እንደሚገኙ የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ ፅፈት ቤት አስታውቋል።

የአሁኑ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በትራንስፖርት፣ በወደብ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በጉምሩክና በንግድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።

የጋራ ኮሚሽኑ የሁለቱ አገሮች የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር ይመክራል፤ ባጋጠሙ ችግሮች ላይም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy