Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

0 679

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር አላስቴይር ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በትብብር እንደሚሰሩ ተስማምተዋል።

ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያና እንግሊዝ ታሪካዊና ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ስትራቴክ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ገልጸው ይህን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት በትብብር ይሰራሉ ብለዋል።

ሁለቱ አገሮች አሁን ያለውን ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል ትስስር ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ በትብብር በመስራት ላይ መሆናቸውን ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ሁለቱ አገሮች በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ተመሳሳይ ራዕይ አንግበው በትብብር እየሰሩ ይገኛሉም ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ እና ስለተገመዘገቡ ውጤቶች እንዲሁም ስላጋጠሙ ተግዳሮቶች በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል። እንግሊዝ እያደረገችው ስላለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍም ምስጋናችውን አቅርበዋል ።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አላስቴይር ዲቪድ ማክፌይል በበኩላቸው እንግሊዝ በኢትዮጵያ የመጣውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ ታደንቃለች ድጋፏንም አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሰላም አንዲሰፍን እጫየወተች ያለውን ሚናም እንግሊዝ ተዳንቃለች በዚህ ዙሪያ ከኢትየጵያ ጋር ያላትን ትብብርም አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

አምባሳደሩ በመቀጠልም በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሁለቱን አገሮች የቆየ ወዳጅነትና ትብብር አጠናክረው ለማስቀጠል እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
እንግሊዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ልማት በገንዘብ ከሚደግፉ አገሮች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች።

አትዮጵያና እንግሊዝ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱት በ1889 ዓ.ም ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ምንጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy