Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ

0 1,506

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ መመስረቱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

ተከሳሾች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የቂሊንጦ፣ የዝዋይ እና የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 3 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረፊያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት ከኃላፊዎች በተሰጠው ትዕዛዝ ማንነታቸው ባልተለየ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት በታራሚዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት እና ህይወት ህልፈትን አስከትሏል፡፡

በተፈጠረው የማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያት ከ400 በላይ የሚሆኑ በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎችን ወደ ሸዋሮቢት ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱ በማድረግ የነበራቸውን ንብረት በመቀበል በባዶ እግራቸው በቁምጣ ብቻ በመኪና ላይ እንዲጫኑ በማድረግ፤ ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ሲደርሱም በመስመር በማሰለፍና በማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በዱላ በመደብደብ፣ 175 የሚሆኑ ታራሚዎችን ደግሞ ባዶ ቤት የሴሚንቶ ወለል ላይ እንዲተኙ በማድረግ፣ ለሁለት ለሁለት በካቴና በማሰር ለረዥም ጊዜ በማቆየት፤ በካቴና እጃቸውን ሁለት ሁለት እያደረጉ በማሰር በባዶ እግራቸው መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ እጃቸውን ሳይታጠቡ ምግብ እንዲመገቡ እና ህክምና በመከልከል እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምርመራ ጨርሰው ወደ ሌላ ክፍል ሲዘዋወሩ ለ42 ቀናት ከአልጋ ጋር ለ24 ሰዓት በካቴና በማሰር፣ 37 የሚሆኑ ተበዳዮች ፍርድ ቤት ረበሻችሁ በማለት ከ3 እስከ 6 ወር እጃቸውን በካቴና አስሮ ጨለማ ቤት ውስጥ በማሰር፣ ግለሰቦች የለበሱትን ልብስ በማስወለቅ ቲሸርትና ቁምጣ በማስለበስ እና በፌሮ ብረት እንዲደበደቡ በማድረግ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ያደረጉ በመሆኑ በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ተከሰዋል፡፡
የተከሳሽ ጠበቆች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የተከራከሩ ቢሆንም የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡
ተከሳሶችም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ የመሰረተባቸው ክስ በችሎቱ ተነቦ ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይዘው ለመቅረብ ለየካቲት 27/20011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy