Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

0 819

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

(ኢ.ፕ.ድ)

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደወላቡና ደሎመና ወረዳዎች ተገኝተው የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው በመደወላቡ ወረዳ የተገነባውን የመደወላቡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በደሎመና ለሚገነባው የመስኖ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ታውቋል።

በምክትል ፕሬዝዳንቱ የመሰረተ ልማት ጉብኝት ላይ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መሳተፋቸው ተመልክቷል።

አቶ ሽመልስ በትናንትናው ዕለት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በባሌ ሮቤ ከተማ ከሕብረተሰቡ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy