Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ

0 772

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ
*
(ኢ.ፕ.ድ)

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንንና ከአማራ ክልልላዊ መንግሥት ርዕስ መስተዳድር አምባቸው መኮንን ጋር በመሆን ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2011 ውይይት አካሄዱ::

በንግግራቸው ወቅት ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የክልሉ ነዋሪዎች በልዩነቶች መካከል በሰላም፣ በፍቅርና በይቅርታ ተቻችሎ የመኖር ባሕል አድንቀዋል::

የውይይቱ ተሳታፊዎች በርካታ ከሕግ የበላይነት፣ ከመሠረተ ልማት፣ ከሥራ ፈጠራ:፣ ከክልላዊ የበጀት ድልድልና ከማኅበራዊ አካታችነት ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን አንሥተዋል::

ለትነሡት ጥያቄዎች መልስ የሰጡት ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ስኬቶችን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አንሥተው ወደ ሕግ ፊት የቀረቡ 4 ሺህ ያህል የሚሆኑ ግለሰቦች መኖራቸውን ገልጠዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራን አስታውሰዋል:: ጠ/ሚሩ ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ለመሠረተ ልማት የሰጠውን ትኩረት በተለይም መንገድንና በደሴ ከተማ የሚሠራውን የሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ ጠቅሰዋል::

በውይይቱ ማጠናቀቂያ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በመደመር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል:: በወቅቱም ሁሉም ከፋፋይ ሐሳቦችን በማስወገድ በአንድነትና በተባበረ ክንድ ድህነትን ለማሸነፍ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል::

ለአረንጓዴና ጽዱ ኢትዮጵያ ያላቸውን ቁርጠኝነትን በተመለከተ ከምክትል ጠ/ሚርና ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመሆን በ1890ዎቹ መጨረሻ በንጉሥ ሚካኤል በተገነባው አይጠየፍ አዳራሽ ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል::

ምንጭ:- የጠ/ሚር ፅ/ቤት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy