Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከተማ አስተዳደሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በቀን 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ለተያዘው እቅድ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

0 2,261

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከተማ አስተዳደሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በቀን 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ለተያዘው እቅድ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ በቀን 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ለተያዘው እቅድ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈጽ ቤት ፕሬስ ሴክረተሪ ወይዘሪት ፌቨን ተሾመ በከተማ አስተዳደሩ ሃምሌ 22 ቀን 2011 ለችግኝ ተካላ በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም በመዲናዋ 116 ወረዳዎች ወጣቶችን በማሳተፍ 2ነጥብ8 ሚሊየን ጉድጓዶች የተዘጋጁ ሲሆን ለዚህ ፕሮግራም ከ400 በላይ የመትከያ ሳይቶች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ፕሮግራም የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ሚሳተፉበት ቦታ መዘጃጀቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በዕለቱ የሚሰሩ ስራዎችን የሚመራ ግብረ ሃይል የተቋቋመ ሲሆን 100ሺ ያህል ወጣቶች የእለቱን ፕሮግራም ዝግጅት የሚያስተባብሩ ይሆናል ነው ያሉት፡

ሰፋፊ የመትከያ ቦታ የሌላቸው አራዳ ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ወረዳ ነዋሪዎች ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በወረዳቸው በመገኘት ችግኞችን በመውሰድ በጊቢያቸውና በ20/50 ራድየስ መትከል ይችላሉ ብለዋል፡፡

በማስፋፍያ አከባቢ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በየአከባቢዎቻቸው በተዘጋጁ የመትከያ ጣቢያዎች እንደሚተክሉ ነው የተናገሩት፡፡

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የችግኝ ተከላ ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለአገልግሎት እንደማይሰጡም ገልጸዋል፡፡

የከተማው ነዋሪ ለከተማው ያለውን ፍቅርና በጎ አመለካከት ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲገልፅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ማቅረቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy