ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
**********************************
(ኢ.ፕ.ድ )
ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉበኤውን እያካሄደ ነው፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ በጉባኤው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ እንዳሉት÷ በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር እና የህግ የበላይነት እንድርጋገጥ ባለፈው አመት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።
የክልሉን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማርጋገጥ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት አፈ ጉባኤዋ የክልሉ መንግስት የተገኘውን ለውጥ ለህዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ ባለበት ሁኔታ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ አካላት ሂደት በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በጨፌው የተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት የሚደርግ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የ2011 የክልሉን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
ጨፌ ኦሮሚያ በዚህ ጉባኤው በክልሉ የ70 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ያጸደቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ በሀገሪቱ በፖለቲካው መስክ የተገኘውን ድል ወደ ኢኮኖሚው ለማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና ሹመቶችን መስጠትም ከጉባኤው ይጠበቃል።
ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ መመሪያዎች እና ደንቦችም ይጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
ጨፌው ባለፈው በጀት አመት 16 የተለያዩ ደንቦች እና መመሪያዎችን በማጽደቅ በተለያዩ አማራጮች ለክልሉ ስራ አስፈፃሚዎች እና ህዝብ እንዲደርስ ማድረጉንም አፈ ጉባኤዋ አስታውሰዋል፡፡