Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው” ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

0 1,052

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

”ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው” ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

(ኢ.ፕ.ድ)

ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 9 ሺህ 637 ተማሪዎች ዛሬ ባስመረቀበት ወቅት ነው።

በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ብለዋል።

ተመራቂዎቹ እዚህ ለመድረስ ሳይማሩ ያስተማሯቸው ቤተሰቦቻቸው፣ በብዙ መስዋእት ያስተማሯቸው አስተማሪዎቻቸው እና ከበጀቷ ትልቁን በጀት የመደበችላቸው ሀገራቸው ብዙ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈለችላቸው ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኑሮ ቀንበር ሳይደናገጡ የተከፈለላቸውንም ዋጋ ዋጋ ሳያሳጡ እዚህ መድረሳቸው ለትውልድ መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደሚቻል ማሳያም ነው ብለዋል፡፡

ትልቁ እውቀትን መሸመቻ መድረክ ትምህርት ቤት ቢሆንም ተመራቂዎች ከዩኒቨርስቲ ለቀው ቢውጡም ትምህርት እንደማያቆም የተናገሩት ዶክተር አብይ ተማሪዎቹ ለትዳር፣ ለስራ እንዲሁም ለህይወት ፈተናና ትምህርት እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በቂ ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy