Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እስራኤል በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስርዓት ይፋ ለማድረግ እየሰራች ነው

0 2,159

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

እስራኤል በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስርዓት ይፋ ለማድረግ እየሰራች ነው

(ኢፕድ)
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ እስራኤል በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስርዓት ይፋ ለማድረግ ከመንግስትጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ተናገሩ።

አምባሳደሩ እንዳሉት በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ምርታማነቱ እንዲጨምር ለማድረግ ያላትን ልምድ ተጠቅማ እየደገፈች ነው ብለዋል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእስራኤል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የሁለቱ ሀገራት ቀጣይ ግንኙነት ፍኖተ ካርታ ላይ ስምምነት መድረሳቸውን አንስተዋል፡፡

ሽብርተኝነትን እና ፅንፈኝነትን በጋራ ለመዋጋትም በሃገራቱ የፀጥታ አካላት በጋራ ይሰራል ብለዋል።

በተለይም በፀጥታ ሃይል ስልጠና እና ቅድመ መከላከል ላይ ባተኮረ አካሄድ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ሽብርተኝነትን እና አክራሪነትን ለመዋጋት በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን ግብርና ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ውስጥ በግብርና ማምረቻ መሳሪያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ከፍተኛ ቀረጥ ትልቅ ፈተና እንደነበረም አስታውሰዋል።

አሁን ላይ ተጥሎ የነበረው ቀረጥ መነሳቱ ለሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ መጭው ጊዜ ብሩህ መሆኑን አመላካች መሆኑንም አንስተዋል።

ላለፉት 30 ዓመታት እየሰራችበት ያለው የግብርና ዘርፍ በተለይ በኢትዮጵያ የአቮካዶ ምርትን ለማሳደግ ያደረገችው ጥረት አነስተኛ ማሳ ያላቸውን የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛልም ነው ያሉት።

በቀጣይም አዲስ እና ዘመናዊ የመስኖ ልማት ስርዓት ይፋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አምባሳደሩ እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በግብርናው ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎች ላይ የተሳሰረ መሆኑንም ያነሳሉ።

በጤናው ዘርፍ በተለይም ድንገተኛ ወረርሽኝ ሲከሰት እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ በመድሃኒት አቅርቦት እና ከአምቡላንስ ስምሪት ጀምሮ ያለውን ስራ በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

እንደኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ኢትዮጵያ ከስነ ምህዳሯ ጋር ተስማሚ የሆነ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንድትጠቀም እስራኤል በቅርበት እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy