በኢትዮጵያ ለ1 ወር የተከናወነው የጸሎት መርሐ ግብር ዛሬ ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ለአንድ ወር የተከናወነው የጸሎት መርሐ ግብር ዛሬ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች ባዘዙት መሠረት ለአንድ ወር የተከናወነው የጸሎት መርሐ ግብር በዐርበኞች ቀን ተጠናቅቋል” ብለዋል።
የጸሎት መርሐ ግብሩ ብዙ መንፈሳዊ ሀብቶች እንዳሉ ማሳየቱንም ገልፀዋል።
በጸሎት መርሐ ግብሩ ያሳየነውን ትብብርና ትጋት የዚህችን ሀገር ችግር ለዘለቄታው ለማስወገድ ከተጠቀምንበት ትልቅ ኃይል መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።
መርሐ ግብሩን ያዘጋጁ፣ ያስተባበሩና በሚዲያ ያስተላለፉ ሁሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስግነዋል።