Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር መንግስትን እየፈተኑ የሚገኙ ችግሮችን በጋራ መሻገር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር መንግስትን እየፈተኑ የሚገኙ ችግሮችን በጋራ መሻገር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

0 2,126

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር መንግስትን እየፈተኑ የሚገኙ ችግሮችን በጋራ መሻገር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር መንግስት በሚያደረገው ጥረት መልካም ጅምሮች ቢኖሩም፤ በተግባር ሂደት እየፈተኑ የሚገኙ ችግሮችን በጋራ በመረባረብ በፍጥነት መሻገር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም አስመልክቶ ከክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቪዲዩ ውይይት አድርገዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለጥንቃቄ የሚሰጡ መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ የሚስተዋሉ ውስንነቶች እና ችግሩን አቅልሎ የማየት አዝማሚያ ፈጣን የባህሪ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መስራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው ወረርሽኙን ለመግታት የሚያግዙ አደረጃጀት ፈጥረው አዋጁን ተከትሎ የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተግባር ሂደት በየደረጃው የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት በቀጣይ ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል እና የከፋ ዋጋ እንዳያስከፍል በጋራ እንደሚረባረቡ ገልፀዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy